Ethiopian Meat and Dairy Industry Development Institute,
Market Development Directorate
- Develop Marketing Strategies, Programs, and Tactics for Market Expansion, and Provide Professional Support;
By analyzing the marketing environment (PESTLE) of the selected destination country, the directorate provides market information for the subsector industry with a view to satisfying stringent requirements. The producers at the subsector have been able to identify the types of support they need to be supported by the government and the development partners in their efforts to help them participate in selected national and international exhibitions and trade fairs which enable them to augment their market share. Moreover, market development Directorate facilitates and creates market alliance environment with international buyers in order to make the purchase and create the joint venture.
- Provide factor (input) market and product market linkage support that strengthen the industry’s competitiveness.
Conduct gap based studies and research to identify the gap of sub sector industry quantity of input supply demanding and marketing problems of the sector.Work for the support of both suppliers and industries along the value chain by formulating strategies, laws, regulations, manuals and etc.
The directorate also supports subsector industries in the market linkage, input supply and gives training, workshops, and seminars. In addition to this search best experiences that can make the sub sector industries competitive in international market by price, quality, quantity and delivery time of supply and share for the sector’s industries
በኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት በገበያ ልማት ዳይክቶሬት የሚሰጡ የድጋፍ ማዕቀፎች
- የገበያ ማስፋፊያ ስትራቴጂዎችን፣ ፕሮግራሞችን እና ስልቶችን በመንደፍ ድጋፍ ይሰጣል፤
ለኢንዱስትሪ ምርቶች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን በመፍጠር በአለም ገበያ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ለማስፋት የሚያስችሉ ሀገራችን ከሚታሟላ አስገዳጅ መመዘኛ አንፃር በተመረጡ አገሮች ማክሮ የገበያ ሁኔታዎችን(ኢኮኖሚ፣ማህበራዊ፣ፖሎቲካዊ፣ቴክኖሎጂ፣ ወዘተ) በማጥቱ የተገኙትን የገበያ መረጃዎችን ለንዑስ ዘርፉ ኢንዱስትሪዎች እንሰጣልን፤
በንዑስ ዘርፉ ኢንዱስተሪው የተሰማሩ አምራቾች በተመረጡ ሀገራዊ እና አለምአቀፍዊ ኤግዚቢሽኖችና የንግድ ትርዒቶች ላይ እንዲሳተፉ በማስተባባር በሚሳተፉበት ወቅት የሚያስፈልጋቸውን የድጋፍ አይነቶች በመለየት መንግስት እና የልማት አጋሮች በሚችሉት አቅም ድጋፍ እንዲያደርጉላቸዉ በባለቤትነት እናስተባብራልን፡፡ የንዑስ ዘርፉን ኢንዱስትሪ ምርቶችን ለመግዛትም ሆነ በትብብር አብሮ ለመስራት ከውጭ የሚመጡ ገዢዎችን ከአምራቾች ጋር በማገናኘት፣ በማደራደርና በማስማማት የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ያደርጋል፣
- የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ የግብዓት አቅርቦት፣ የምርት ትስስርና የምርት ቅብብሎሽ የድጋፍ ሥራዎችን ያከናዉናል፤
የንዑስ ዘርፉን አምራቾች የግብዓት ፍላጎትና የአቅርቦት ክፍተትን በተመለከተ መነሻ ችግሮች ላይ በመመስረት ክፍተቱን ለመሙላት የሚያስችል ጥናት በማከናወን የጥናቱንም ዉጤት አግባብ ላላቸዉ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን እንሰራለን፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የግብዓት አቅርቦትን፣ የቅብብሎሽን እና የትስስር ሥርዓቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመዘርጋት የሚያግዙ ስትራቴጂዎችን፣ ህጎችን፣ መመሪያዎችን፣ የአሠራር ስልቶችን በማዘጋጀት ተጠቃሚዎች ሥራ ላይ እንዲያዉሉት፤ እንዲሁም የግብዓት አቅርቦት ቅብብሎሽንና የትስስር ሥርዓትን በተፈለገው ደረጃ ለማካሄድ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን፣ ወርክሾፖችን፣ ሴሚናሮችን እናዘጋጀለን፡፡ በሌላ በኩል የኢንዱስትሪ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ከብዛት፣ ከጥራት፣ ከዋጋና ከማቅረቢያ ጊዜ አንጻር ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገኙ የሚያግዙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለንዑስ ዘርፉ ኢንዱስትሪዎች እናስተላልፋል፡፡